Friday, May 20, 2016

ዓለም አቀፉ የሙዚየም ቀን ተከበረ



 የዘንድሮ የዓለም የሙዚየም ቀን‹‹ ሙዚየሞችና ባህላዊ መልክዓ ምድር!››/ Museums and Cultural Landscape/ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ጊዜ በአገራችን 14 ጊዜ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተከበረ፡፡
በተፈጥሮአዊና ባህላዊ የመልክዓ ምድር አያያዝና አጠቃቀም ፣ በጥምር ደንና የግብርና ሥርዓት  በዓለም ቅርስነት ባስመዘገበው በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መከበሩ ልዩ ያደርገዋል፡፡  በክልሉ ከተማዎች ማለትም  በሐዋሳ ፣ በአርባ ምንጭ ፣ ቱርሚ፣ በጅንካና በኮንሶ አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ ከግንቦት 06   እስከ ግንቦት 12  2008 . የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውነዋል፡፡

Tuesday, May 10, 2016


በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ የዘገባ ስራዎችን የሚያግዝ ስልጠና

ለሚዲያ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው፡፡

የተለየ ትኩረት እያገኘ የመጣውን የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በተገቢው መልኩ ለማስተዋወቅ እንዲቻል የሚረዳ ስልጠና በአዳማ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ከግንቦት 2-10/2008 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ ስልጣና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡ ስልጠናው በዘርፍ ያለውን የባለሙያዎች የግንዛቤ ክፍተት ይሞላል ተብሎ የታሰበ እና በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በቱሪዝምና ሚዲያ ፎረም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ዓመታዊውን የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን ማጠናቀቂያ ፌስቲቫል

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተካሄደ፡፡

 

በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የማርች ወር የሚከበረው የዱር እንስሳት መጠለያዎች ቀን በኢትዮጵያም ባለፉት ሰላሳ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የምታከብረው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአንድ ወር ያክል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉን ስታከብር ቆይታ ሚያዝያ 29-30/2008 ዓ.ም. ለሁለት ቀናት በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የማጠቃለያ ፊስቲቫል አዘጋጅታለች፡፡