Tuesday, November 17, 2015


ድሬደዋ በሀገር ደረጃ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን እያስተናገደች ነው፡፡





እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንሳና ባህል ድርጅት በወሰነው መሰረት በየዓመቱ ኖቨምበር 16 ቀን የዓለም የመቻቻል ቀን ሆኖ በአባላ ሀገራቱ ይከበራል፡፡ አባል ሀገራቱም በዓሉን በተለያየ መልኩ ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡ ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህንን በዓል ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ከህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆይ ዝግጅት እያከበረችው ነው፡፡


ለስድስተኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን በዓል ድሬደዋ ከተማ እያስተናገደችው ሲሆን ዝግጅቱን በዋናነት ያዘጋጀው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዳይሮክተሬት ነው፡፡

በዓሉ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያካተተ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ በመቻቻል እሴቶቻችን ዙሪያ የሚያተኩሩ የጥናት መነሻዎች ላይ ከተደረጉ ውይይቶች በተጨማሪም በመቻቻል እሴት ማዕከልነቷ የምትታወቀው ድሬደዋን የመጎብኘት መርሐ ግብርንም ያካተተ ነው፡፡ የዘንድሮው በዓል መሪ ቃልም "በብዝሃነት የፈጠርናቸው የመቻቻል እሴቶች ለልማታችን!" የሚል ነው፡፡

No comments:

Post a Comment