ድሬደዋ በሀገር ደረጃ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የመቻቻል ቀን
እያስተናገደች ነው፡፡
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንሳና ባህል ድርጅት በወሰነው መሰረት በየዓመቱ
ኖቨምበር 16 ቀን የዓለም የመቻቻል ቀን ሆኖ በአባላ ሀገራቱ ይከበራል፡፡ አባል ሀገራቱም በዓሉን በተለያየ መልኩ ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡
ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህንን በዓል ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ከህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆይ ዝግጅት እያከበረችው ነው፡፡