ሜሮን ታምሩ
ከሰኔ 5 እስከ 7 2007 ዓ.ም. በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ሳምንት ልማታዊ ባህሎቻችን
ለህዳሴ ጉዟችን ስኬት! የሚል መሪ ቃል አንግቧል፡፡ የባህል ሳምንቱ በባህሉ የሚኮራ፣ በማንነቱ የሚመካ፣ ትውልድ በመፍጠር
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና መጤ የሆኑ ጠቃሚነት የሌላቸው ባህሎች መከላከልና ወደ ልማት የሚመጣ ህብረተሰብ መፍጠር፣ የኪነ-ጥበብ ዘርፉ
አሁን ከደረሰበት ደረጃ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ማራመድ መቻል እንዲሁም ባህሎቻችንን ከማሳደግ ጎን ለጎን አገራችን ኢትዮጵያ
የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ እንደመሆኗ እንዲሁም አዲስ አበባ የአገራችን ርዕሰ መዲና ከመሆኗ ጋር በተያያዘ በርካታ ባህሎች
ከተማችን ላይ ይንፀባርቃሉ ያለባበስ፣ የአጋጊያጥ የአመጋገብ ስርዓቱ እርስ በእርስ በማገናኘትና በማዋሀድ የተሻለ ባህል እንዲኖር
ያግዛል፡፡