በባህል ዘርፍ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ሊመሰረት
ነው፡፡
አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሯል፤
በሃገራችን የባህል ዘርፍ ላይ የሚሰሩ
ተቋማትን የሚያካትት የምክክር መድረክ ለማቋቋም ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጠራው ጉባኤ ላይ ከዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራ
የሚሰሩ ተቋማትና ግለሰቦች ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በተደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ተካፍለዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች
በቀረቡ የመነሻ ጽሑፎች የባህል ፕላት ፎርም ምስረታ ዓላማዎች፣ በቋንቋና ባህል እሴቶች እና በባህል ኢንዱስትሪ ዘርፎች ሃገሪቱ
በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ውጥኑ የአለመቻቸውን ግቦች የተመለከቱ መነሻ ጽሑፎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በተለያየ አግባብ ለማህበራዊ ትርፍና
ለኢኮኖሚያዊ ትርፍ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በጥቅሉ ባህል ላይ ያተኮሩ ስራዎችን የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን በሙሉ
ያካተተ የጋራ መድረክ ለመፍጠር እንዲቻል ስራውን የሚያከናውኑና የሚያመቻቹ አስራ አምስት አባላት በአመቻች ኮሚቴነት ተመርጠዋል፡፡
የተመረጠው ኮሚቴ አጠቃላይ የሆኑ
የመመስረቻ ስራዎችን በማከናወን ብሔራዊ የባህል ባለድርሻ አካላት ምስረታ ጉባኤ አባላትን ለመጥራት አቅዷል፡፡
No comments:
Post a Comment