Thursday, October 18, 2012
Tuesday, October 9, 2012
በባህል ዘርፍ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ሊመሰረት
ነው፡፡
አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሯል፤
በሃገራችን የባህል ዘርፍ ላይ የሚሰሩ
ተቋማትን የሚያካትት የምክክር መድረክ ለማቋቋም ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጠራው ጉባኤ ላይ ከዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራ
የሚሰሩ ተቋማትና ግለሰቦች ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በተደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ተካፍለዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች
በቀረቡ የመነሻ ጽሑፎች የባህል ፕላት ፎርም ምስረታ ዓላማዎች፣ በቋንቋና ባህል እሴቶች እና በባህል ኢንዱስትሪ ዘርፎች ሃገሪቱ
በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ውጥኑ የአለመቻቸውን ግቦች የተመለከቱ መነሻ ጽሑፎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በተለያየ አግባብ ለማህበራዊ ትርፍና
ለኢኮኖሚያዊ ትርፍ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በጥቅሉ ባህል ላይ ያተኮሩ ስራዎችን የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን በሙሉ
ያካተተ የጋራ መድረክ ለመፍጠር እንዲቻል ስራውን የሚያከናውኑና የሚያመቻቹ አስራ አምስት አባላት በአመቻች ኮሚቴነት ተመርጠዋል፡፡
የተመረጠው ኮሚቴ አጠቃላይ የሆኑ
የመመስረቻ ስራዎችን በማከናወን ብሔራዊ የባህል ባለድርሻ አካላት ምስረታ ጉባኤ አባላትን ለመጥራት አቅዷል፡፡
Wednesday, October 3, 2012
ማጫወት፣ መጋበዝ እና መውደድ የሚችለው የቤኒሻንጉል ጉምዝ
ህዝብ
120 ሰዓታትን በደስታ
የ2005 ዓ.ም የዓለም
ቱሪዝም ቀን መስከረም 17 ቀን ተከብሯል፡፡ ሃገር አቀፍ ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተከበረ ሲሆን ከተከበረባቸው ስፍራዎች
አንዱ ደግሞ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ምድር ነው፡፡ ቱሪዝም ከዘላቂ የሃይል አቅርቦት ልማት ጋር ተቆራኝቶ እንዲከበር በመሪ ቃልነት
የተከበረውን የዘንድሮ የቱሪዝም ቀን ለመታደም ቤኒሻንጉል ጉምዝ ከትመን ነበር፤
ከመተከል ዞን የጀመረው የሞቀ አቀባበል፣ እስከ ኦሮምያ ክልል ድንበር በዘለቀው የሽኝት
ሥነ-ሥረዓት የ120 ሰዓታት እድሜ ነበረው፡፡ በዚህ እድሜ ውስጥ በዙምባራ ጥኡም ዜማ ታጅቦ የጉምዝ አያሌ ባህሎች ከልባችን ገብቷል፡፡ የበርታ እንግዳ አቀባበል፣ የኮሞ ጨዋታ የማኦ መስተንግዶ ስለቤኒሻንጉል ጉምዝ
የምናወራውን እልፍ አድርጎታል፡፡
የቦሮ ሽናሻ ብሄረሰብ ከድንቅ ውዝዋዜው ጋር ቁርጡን እየመተረ መስቀሉን አብረንው እንድንታደም አድርጎናል፡፡ የማንኩሽ
መስተንግዶ፣ የደጃዝማች ባንጃው ድንቅ እልፍኝ፣ የህዳሴው ምድር ውሎ አያሌ ትዝታዎች የታጨቁበት ጉዞ እንዲሆን አድርገውታል፡፡ ሀብታሙ
ክልል አረንጓዴ ምድር እና ገና ያልተነገረ ታሪክ ያለው ነው፡፡
ተጫዋቹ፣ ተግባቢውና ለሰው ቅርብ የሆኑት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ከተገናኘንበት ቀን ጀምሮ እንግዳ ተቀባይ ህዝብ
ብቻ ሳይሆን እንግዳ ተቀባይ አመራር እንዳለ አብነት ሆነው አሳይተውናል፡፡ ያዓ መሰራ እኩል ቀን ከገደልንባቸው መዳረሻዎች አንዱ
ነበር፡፡ የሼህ ሆጀሌ ቤተ-መንግስት ጉብኝት የማንጎ ሎጅ መስተንግዶ እና መሰል የመዝናኛ ጊዜዎች አይረሴና መልካም ነበሩ ዓመቱን
እንደ ወቅቱ እየቆነጠርን ለመተንተን እድሜና ጊዜ ይስጠን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)