ኢትዮጵያ በብሄራዊ ሀዘን ላይ ትገኛለች፤
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስክሬን ትናንት ምሽት
ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብቷል፤
መንግስት መደበኛ የመንግስት ስራ ሳይዘጋ የሃዘን አዋጁ እንዲቀጥል
አውጇል፤

ሰኞ ለማክሰኞ ዋዜማ ከእኩለ ለሊቱ በፊት መሞታቸው የተነገረው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ
ዜናዊ በስልጣን ላይ በቆዩባቸው 21 ዓመታት የሚመሩት መንግስት ሀገራችን የቱሪዝምና የባህል ፖሊሲዎች እንዲኖሯት በማድረግ፣በውጭ
ጉዳይ ፖሊሲ ስኬት የኮንፈረንስ ቱሪዝም እንዲስፋፋ፣ አዳዲስ ፓርኮች እንዲለሙ፣ ቅርሶች የቅርሱ ባለቤት የሆነው ህዝብ እንዲያስተዳድራቸው
በማድረግ እና የቱሪዝም ልማቱን የሚያግዝ የብድር ስምምነት በማድረግ ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ላይ በማተኮር፣ በርካታ የባህል ልውውጥ
መድረኮችን ሀገራችን እንድትሳተፍ በማስቻል ያበረከቷቸው ተግባራት የሚወደሱ ናቸው፡፡
የሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን እና የቱባ መጽሔት ባልደረቦች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ሞት የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለባለቤታቸው፣ለትግል ጓዶቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን፡፡