ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን ገመገመ
ብዙዎቹ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግበዋል፡፡
ፓርኮችን በመጎብኘት ረገድ የሃገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
የባህል ልውውጥና ግንኙነት አፈጻጸሙ 108 በመቶ ሆኗል….
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘጠኝ ወራት
አፈጻጸሙን በመገምገም የአፈጻጸም ልኬቱን በቁጥርና በመቶኛ አስቀምጧል፡፡ በዘጠኝ ወሩ አስራ ሶስት የባህል ልውውጥና ግንኙነት ለማከናወን
ታቅዶ የነበረ ሲሆን አስራ አራት ለማከናወን በመቻሉ ከእቅዱ ያለፈና 108 በመቶ የሆነ ውጤት ለማስመዝገብ ተችሏል፡፡ በግማሽ ዓመቱ
ብቻ 9 የባህል ልውውጥና ግንኙነት ለማከናወን ታስቦ 11 ለማከናወን ሲቻል አንድ ባህላዊ የሙዚቃ ኪነት ቡድን በውጪ ሃገር ትርኢት
ለማቅረብ በታሰበው መሰረት በህንድ ሶስት ከተሞች ትርኢቱን በማሳየት ሃገሪቱንና የህዝቦቿን እሴት በሚገባ ለማስተዋወቅ ተችሏል፡፡
በዘጠኝ ወራቱ አፈጻጸም የቱሪስቶች
ቁጥር 474,249 ደርሷል፤ ይህም ከእቅዱ አንጻር 88 በመቶ ሲሆን በቋሚ ኤግዚቢሽን ጎብኚዎች ረገድ 106,084 የሀገር ውስጥና
የውጪ ጎብኚዎች በብሄራዊ ሙዚየም የቋሚ ኤግዚቢሽን የማስጎብኘት እድል ተፈጥሯል፡፡ በሃገር ውስጥ ጎብኚዎች ገረድም በተለይም ፓርኮችን
በመጎብኘቱ አበረታች ውጤት የተመዘገበ ሲሆን 30,110 የሃገር ውስጥ ጎብኚዎች የሃገሪቱን ፓርኮች ጎብኝተዋል፡፡ የሴቶቹ ቁጥር
ደግሞ 12,405 ነው፡፡ ይህ ቁጥር 42,246 የውጪ ጎብኚዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር የሃገር ውስጥ ጎብኚዎች ፓርኮችን የመጎብኘት
ባህል እያደገ መምጣቱን ያሳያል፡፡
በአጠቃላይ በአለፍት ዘጠኝ ወራት ከቱሪስቶች 371,811,216 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ የአንድ
ቱሪስት አማካኝ የቆይታ ግዜ 6.5 ሲሆን የቀን ወጪው ደግሞ 120.6 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን ያገኘንው መረጃ ያመላክታል፡፡
No comments:
Post a Comment