የአቡኑ ከተማ
በሰሜን ሸዋ ዞን .. ከደጋማው የመንዝ ምድር .. ተፈጥሮው በብዙ ከሚተርክበት
.. መልከአ-ምድር መሃል በዚያ ንጹህ አየር በሚሳብበት ውብ ምድር የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡
ሰላድንጋይ የዚህ ድንቅ ስፍራ መጠሪያ ነው፡፡ ከሰሜን ሸዋ ዞን መዲና
ከደብረ ብርሃን ከተማ በ75 ከ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሰላ ድንጋይ ኢትዮጵያን ለ38 ዓመታት በፓትሪያሪክነት ያገለገሉት አባት
የአቡነ ማቴዎስ የመንበር ጵጵስናቸው መቀመጫ ነበረች፡፡
ግብጻዊው
ፓትሪያሪክ አቡነ ማቴዎስ በዚሁ ስፍራ በ1875 ዓ.ም የማርቆስ ቤተ-ክርስቲያንን አሰርተዋል፡፡