gondar/ጎንደር |
ሃገራችን ኢትዮጵያ የጎብኚዎችን ቀልብ ለመሳብ የሚችሉ በርካታ ልዩ ልዩ ገፅታዎችን ከታደሉ ጥቂት የዓለማችን ሃገሮች አንዱዋ ነች፡፡ የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔዋ አሻራ የሆኑ ብዙ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮዓዊ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች አሏት፡፡
ከዚህ ሌላ ከ80 በላይ የሆኑ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሰላምና በመቻቻል የሚኖሩበት ሃገር በመሆንዋ የብሄረሰቦችና ቋንቋዎች ሙዝየም ለመባል በቅታለች፡፡ ሃገራችንን በአለም ላይ ታዋቂ ያደረጋት ሌላው ገፅታ ደግሞ የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ህዝቦች በመተሳሰብ አብረው የሚኖሩባት መሆኑ ነው፡፡ ለሃገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችለው ሌላው ገጽታችን ደግሞ ሀገራችን የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት መሆንዋ ነው፡፡
ከዘመን አቆጣጠሩ ጋር ተያይዘው በሃይማኖቶቹ አማንያን በስፋት የሚከበሩት በዓላት /Festivals/ በርካታ ቱሪስቶች ሃገራችን እንዲጎርፉ የማድረግ አቅም አላቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ሃገራችን እንግዳ ተቀባይ፤ የሰው ዘር መገኛ፤ የነፃነት ተምሳሌት … በሚሉ በጎ ስሞች ትታወቃለች፡፡
ይሁን እንጂ ሃገራችን ዘርፈ ብዙ በጎ ገጽታዎችና የቱሪስት መስህብ ሃብቶች ባለቤት ብትሆንም ከዘርፉ እያገኘች ያለው ጥቅም ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ከሴክተሩ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ያሉንን ታሪካዊ፣ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ የቱሪስት መስህቦችን በስፋት ከማስተዋወቅ ባሻገር በየክልሉ አዳዲስ መስህቦችን መፈተሸና ጥቅም ላይ ማዋል ተገቢ ይሆናል፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ አስደሳችና አስደናቂ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች አሏት፡፡ በሌላው ዓለም ብዙም ያልተለመዱትን ባህላዊ፤ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች ሃገራችን ከአፍሪካ የተለየች የቱሪስት መዳረሻ ሃገር ያደርጓታል፡፡ ለመሆኑ እርስዎ የሃገርዎን የቱሪስት መስህብ ሃብቶች በአግባቡ ያውቃሉ? ለዛሬ ጥቂቶቹን እናስተዋውቅዎ፡፡ ሃገራችን ካሏት ድንቅ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች ውስጥ ስምንቱ በተባበሩት መንግስታት የሣይንስ፣ የባህልና ትምህርት ድርጅት
/UNESCO/ በዓለም ቅርስነት ተመዝግበዋል፡፡
This comment has been removed by the author.
ReplyDeleteለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች የተፈጠሩት በኢትዮጵያ ነው። የሰው ዘር መገኛ ብቻም ሳትሆን ኢትዮጵያ የነፃነት ተምሳሌትም እየተባለች በበርካታ በጎና ማራኪ ስሞች ትታወቃለች፡፡በመጀመሪያ ከተገኙ ህዝቦች ወይም ሰዎች አንዱ ደግሞ የየም ህዝብ ነው፡፡
ReplyDelete