Friday, December 23, 2011

ዕፅዋት



    ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት በደኖች መጨፍጨፍና በተፈጥሮ እፅዋት መመናመን ምክንያት በተከሰተው የመሬት መራቆት ትታወቃለች፡፡ ምንም እንኳን ስለመጀመሪያው የእፅዋት ሽፋን ገፅታ በጥቂቱ ቢታወቅም የሀገሪቱን ሀብታምነት የሚያሳዩ የተፈጥሮ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ በእንስሳት አለም እንዳለው ሁሉ ብዙ እፅዋትም በኢትጵጵያ ብቻ የሚገኙ ሲሆን ሌሎችም ብዙ መገኘት የሚገባቸው አሉ፡፡

Thursday, December 22, 2011

የዱር እንስሳት


wild life in Ethiopia
የዱር እንሰሳት
 በከፍታማው የኢትዮጵያ ክፍል ለብዙ ሚሊዮን አመታት ተለይቶ በተካሄደው ያልተለመደ ክንዋኔ የተለየ ዝርያ ላላቸው ነገሮች መፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይም ጥቃቅን እና ወደ አልተለመደ አካባቢ በጓዝ ያልቻሉ የዚህ ክስተት ያካትታቸዋል፡፡ ሌሎች መካከለኛ የአየር ፀባይ ካለው ክልል የመጡ ዝርያዎች ደግሞ የለመዱትን የሚመስል የመኖሪያ ስፍራ አግኝተው እዚሁ መኖር ችለዋል፡፡

Wednesday, December 21, 2011

ኢትዮጵያ እንደ ቱሪስት መዳረሻነት


gondar/ጎንደር
ሃገራችን ኢትዮጵያ የጎብኚዎችን ቀልብ ለመሳብ የሚችሉ በርካታ ልዩ ልዩ ገፅታዎችን ከታደሉ ጥቂት የዓለማችን ሃገሮች አንዱዋ ነች፡፡ የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔዋ አሻራ የሆኑ ብዙ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮዓዊ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች አሏት፡፡
ከዚህ ሌላ 80 በላይ የሆኑ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሰላምና በመቻቻል የሚኖሩበት ሃገር በመሆንዋ የብሄረሰቦችና ቋንቋዎች ሙዝየም ለመባል በቅታለች፡፡ ሃገራችንን በአለም ላይ ታዋቂ ያደረጋት ሌላው ገፅታ ደግሞ የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ህዝቦች በመተሳሰብ አብረው የሚኖሩባት መሆኑ ነው፡፡ ለሃገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችለው ሌላው ገጽታችን ደግሞ ሀገራችን የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት መሆንዋ ነው፡፡