Thursday, December 31, 2015


የጎንደር ዩኒቨርስቲ 9ኛው የቱሪዝም ሳምንት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው፡፡




ዛሬ በዋናው ካምፓስ የባህል ፌስቲቫል ተካሂዷል፡፡ የሰሜን ጎንደርና አካባቢው መስህቦችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይም ከሰሜን ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር የቀረበ ሲሆን በጎንደር ከተማ ሆቴሎች መካከል የምግብ ዝግጅት ውድድር ተካሂዷል፡፡ የዘንድሮው በዓል መታሰቢያነቱ ለልዑል ራስ መንገሻ ስዩም አደረገ፡፡

Sunday, December 20, 2015



ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት ያከናወነቻቸው
የዘላቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ፡፡
ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር በኢትዮጵያ ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት ላለፉት 6 ዓመታት በአክሱም፣ በላሊበላና በአዲስ አበባና አካባቢዋ ሲከናወኑ የነበሩ ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ 

Thursday, December 10, 2015


                            አሹራ-ሀረሪዎች የሚያደምቁት ኩነት
 
 

አሹራ በሀረሪ በድምቀት የሚከበር ዓመታዊ ኩነት ነው፡፡ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የሆነው ሙሐረም በገባ በ10ኛው ቀን ይከበራል፡፡ አሹራ በሀረሪዎች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በርካታ ባህላዊ ክንዋኔዎች የሚያጅቡት የተለየ በዓል ነው፡፡ የበዓል አከባበሩ የተለየ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች አንዱ በየቤቱ በአዋቾች የሚዘጋጀው ገንፎ በቅቤ አንዱ ነው፡፡


                     ገዜ ጎፋ ወረዳ
 

ገዜ ጎፋ ወረዳ በጋሞ ጎፋ ዞን ከሚገኙ 2 ከተማ አስተዳደሮችና 15 ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ የወረዳው ዋና ከተማ ቡልቂ ስትሆን የተመሰረተችውም በ1918 ዓ.ም. ነው፡፡ የቡልቂ ከተማ ከተማው ወደ ሳውላ እስከ ተዛወረበት ማለትም እስከ 1955 ዓ.ም.  የድሮው የጎፋ አውራጃ ከተማም ነበረች፡፡
የገዜ ጎፋ ወረዳ በስተሰሜን ደምባ ጎፋና መሎ ኮዛ ወረዳዎች፣ በስተምስራቅ ደምባ ጎፋና ኦይዳ ወረዳዎች፣ በስተደቡብ ደቡብ ኦሞ ዞንና ኦይዳ ወረዳ፣ በስተምዕራብ ባስኬቶ ልዩ ወረዳና መሎ ኮዛ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡ ወረዳው ከአዲስ አበባ በ531 ኪሎ ሜትር፣ ከሀዋሳ 319 ኪሎ ሜትር፣ ከአርባ ምንጭ 267 ኪሎ ሜትር፣ ከወላይታ 148 ኪሎ ሜትር ከሳውላ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የወረዳው አየር ንብረት በሶስት አግሮ ኢኮሎጂካል ዞኖች የሚከፈል ሲሆን ደጋ 21.5 በመቶ፣ ወይና ደጋ 70 በመቶ፣ ቆላ 8.5 በመቶ ነው፡፡ አማካይ የሙቀት መጠኑ ደግሞ 23 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሲሆን የዓመቱ አማካይ የዝናብ መጠን 1300 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡