በሀገራችን
ደብቡ ክልል ጋሞ በተባለ መካነ-ቅርስ ከፍተኛ
ስፍራ ሞጣ በሚባል ዋሻ እድሜው 4ሺ 500 ዓመት
የሚገመት “ባይራ” የተሰኘ
የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል
ተገኘ፡፡
ከግኝቱ
ላይ በጥንቃቄ በተወሰደ
ናሙና በእፍሪካ በዕድሜ
ከፍተኛ የሆነውን የዕድሜ
ዘረ-መል አወቃቀር
ማወቅ ተችሏል። የግኝቱን
ስያሜ በተመለከት የጥናት
ቡድኑ የተገኘበትን የጋሞ
ማህበረሰብ ቋንቋ መሰረት
ባደረገ ሁኔታ "ባይራ"
ብሎ የሰየመው ሲሆን
ትርጉሙም የበኩር ልጅ
እንደማለት ነው።