የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ሙዚየም
የልጅ እያሱ አልጋ |
አዲስ አበባ ከሚገኙ 14 ሙዚየሞች አንዱ የቀጨኔ ሙዚየም ነው፡፡ ቀጨኔ ሙዚየም በአስተዳደር
ጊዜያቸው ለህብረተሰቡ ኑሮ ምቹ ከመሆናቸው የተነሳ አቤቶ (ማር) የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ልጅ እያሱ ከመቶ ዓመት በፊት ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ካሳነፁ በኋላ የተቋቋመ
ሙዚየም ነው፡፡ በሙዚየሙ ውስጥ ከሚገኙ ቅርሶች ብዙዎቹ የልጅ እያሱ የግል መገልገያ እቃዎች፣ ነዋየ ቅድሳት፣ አልባሳት እና የተለያዩ
ነገስታት ስጦታዎች ይገኛሉ፡፡