አሸንዳ - የሰሜናዊቷ ኮከብ ከተማ ኮከብ ኩነት
በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
አማኞች ዘንድ
የጾመ ፍልሰታ
ፍጻሜን ተከትሎ
የሚከበረው የአሸንድዬ
በዓል በዋናነት
በሰሜን ኢትዮጵያ
ከሚከበሩ መንፈሳዊ
በዓላት መካከል
የሚጠቀስ ነው፡፡
የአሸንዳ ባህላዊ ጨዋታ መጠሪያ የኾነው ቄጤማ ረዥምና ለምለም እንደ ቅጠል ሰፋ ያለ ሲሆን ቁመቱ ከ80 እስከ 90 ሣ.ሜ ይኾናል፡፡
የአሸንዳ በዓል በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚከበር በሀገራችን ከሚገኙ ኩነቶች አንዱ ነው፡፡
አሸንዳ ጥንታዊና የልጃገረዶች ባህላዊ በዓል ነው፡፡ በተለይም ከአዲስ አበባ በ783 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የክልሉ መዲና
መቐለ በየዓመቱ የምታስተናግደው ይህ ፌስቲቫል ከትግራይ ወጣቶች ባለፈ ጎብኚዎችም በጉጉት የሚጠብቁት ባህላዊ ትዕይንት ሆኗል፡፡