የዛይ ማህበረሰብ የትንሣኤ ዘመን
ዝዋይ የሚለው ቃል ትርጉም ዛይ
ከሚለው የደሴቶቹ ማህበረሰብ መጣ የሚሉ አፈ-ታሪኮች በርካታ ናቸው፡፡ የዝዋይ ደሴቶች እጅግ በርካታ ምሁራንን አፍርተዋል፤ ከዚህ
ዓልፎ እንደ ግርሀም ሀንኮክና ጀምስ ብሩስ ባሉ የጉዞ ጸሐፍት የተተረከላቸው እነኚህ ደሴቶች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን ጋር የጠበቀ ሚስጥራዊ ግንኙነት ያላቸው ናቸው፡፡ ታቦተ ጽዩን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት ስፍራ በመሆኑ ብዙዎች ለበረከት
ይተማሉ፡፡